Shewa Peace & Development Association  ሸዋ ሰላምና ልማት ማህበር (ሸዋሰማ)
  • Home
  • About Us
  • Recent Activities
    • Ataye
    • Building Tomorrow
    • Shewasema Annual meeting
  • Management Team
  • Membership
  • The President's Message
  • Contact Us
Shewa Peace & Development Association  ሸዋ ሰላምና ልማት ማህበር (ሸዋሰማ)
  • Home
  • About Us
  • Recent Activities
  • Management Team
  • Membership
  • The President's Message
  • Contact Us

Our Programs

በሰላም ዘርፍ

ታሪክ፤ ባህልና ስነ-ጥበብ ዘርፍ

ታሪክ፤ ባህልና ስነ-ጥበብ ዘርፍ

  1. የሸዋን ወጣቶች፤ የሃይማኖት አባቶችን፤ ሽማግሌዎችን፤ ባለሃብቶችንና ምሁራንን በማስተባበር የሸዋን ብሎም የሃገራችንን ሰላም እንዲጠበቅ በዕውቀትና በሀብት መደገፍ።
  2. በአጎራባች ወረዳዎች የሚነሱ ግጭቶችን በጥናት በመለየት ዘላቂ መፍትሔ እንዲያገኙ ከመንግስት ጋር በትብብር መሥራት።
  3. የሰላም መድረኮችን በማዘጋጀት ከሀይማኖት አባቶች፤ ከህብረተሰቡ፤ ከባለሀብቶች፤ ከወጣቶችና ምሁራን ጋር ውይይት በማድረግ ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ መደገፍ።
  4. ብየትምህርት ቤቶች የሰላም ክበባትን መፍጠር፤ ማስተማር፤ የነገ የሰላም አምባሳደሮች እንዲፈጠሩ መደገፍ።

ታሪክ፤ ባህልና ስነ-ጥበብ ዘርፍ

ታሪክ፤ ባህልና ስነ-ጥበብ ዘርፍ

ታሪክ፤ ባህልና ስነ-ጥበብ ዘርፍ

  1. የሸዋን ሕዝብ ታሪክ፤ ቅርስ፤ ባህል በመጠበቅ ሰው ሰራሽና የተፈጠሮ ጉዳት እንዳይደርስባቸው ማድረግ።
  2. በሸዋ ሕዝብ ላይ የተፈጠረውን የተዛባ የታሪክ ትርክት ከምሁራን ጋር በመተባበር ምርምር በማከናወን እውነተኛ ታሪኩን ማስተም፤ ማሰራጨት ማስተማር።
  3. የሸዋ ነገስታት ለሀገራችን፤ ለአፍሪካ ብሎም ለመላው ጥቁር ሕዝቦች ያበረከቱትን አስተዋፅኦ በሙዚቃ፤ በፊልም፤ ዶክመንተሪ በማዘጋጀት የተፈጠረውን የተዛባ ታሪክ ማስተካከል።
  4. በሸዋ ነገሥታቶች ስም የባህል ማዕከላትን በመገንባት፤ ተማሪዎች የሚየሚያጠኑበትንና የሚመራመሩበትን ቤተ-መጻሕፍት፤ ሙዚየምና ማስታወሻ ኃውልት ማስገንባት።

በልማት ዘርፍ 

  1. የሸዋ ሕዝበን በገንዘብ/በአይነት፤ ድጋፍ በማድረግ ጥራት ያለው ትምህርት እንዲያገኝ መደገፍ።
  2. የሸዋ ሕዝበን በገንዘብ/በአይነት፤ በመደገፍ የተሻለ የጤና አገልግሎት እንዲያገኝ መደገፍ።
  3. የሸዋ ሕዝብ በመሰረተ ልማት ዘርፍ ተጠቃሚ እንዲሆን ባለሀብቶችን በማስተባበር ከመንግስት ጋር መስራት።
  4. የሸዋን ሕዝብ በግባትና በዕውቀት በመደገፍ በአካባቢ ጥበቃ ንቁ ተሳታፊ በማድረግ የግብርናውን ዘርፍ ምርትና ምርታማነትን እንዲያሳድግ መርዳት።
  5. የሸዋን ሕዝብ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ተጠቃሚ እንዲሆን በግባት በመደገፍ ፈጠራዎችን ማበረታታት (የምንይልክ አዋርድ/ሽልማት በማዘጋጀት ፈጠራን ማበረታታት);
  6. ሕብረተሰቡንና ባለሀብቶችን በማስተባበር በተለያየ መልኩ ጥቃት የደረሰባቸው ወገኖች ከጉዳታቸው አገግመው መልሰው እንዲቋቋሙ ማድረግ።

በኢንቨስትመንት ዘርፍ

  1. የሸዋ ባለሀብቶች በግለም ይሁን በቡድን በኢንቨስትመንት ዘርፍ እንዲሰማሩ የማማከር አገልግሎት መስጠት።
  2. ባለሃብቶችን በሃገራችን የንግድ ሕግ መሠረት በትልልቅና በመካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች በግልም ይሁን በቡድን እንዲሳተፉ የሚገናኙበት መድረክ መፍጠር፤ ማማክርና ማደራጀት።
  3. የሸዋን ሕዝብና ባለሀብቶች በማደራጀት በኢኮኖሚው ዘርፍ ንቁ ተሳታፊና እኩል ተጠቃሚ እንዲሆን ማማከር።
  4. ሸዋ ላይ እየተፈጠረ ያለውን የኢኮኖሚና ኢንቨስትመንት መነቃቃት በፍትሐዊነትና እኩል ተጠቃሚነት እንዲመራ ማማከርና ድጋፍ ማድረግ።
  5. የሸዋን ብሎም የሀገራችንን ዘርፎችን በማስጠናት ከመንግስት ጋር በመተባበር ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ልማትን መደገፍ።

Site Content

የማህበሩ ዓላማ (OBJECTIVE OF THE ASSOCIATION)

 ሸዋ የሰላምና ልማት ማህበር ዋና አላማ በንግድና ኢንቨስትመንት ላይ የተሰማሩ የሸዋን ተወላጅ ባለሃብቶችን፤ ዎጣቶችን፤ ሴቶችን፤ ምሁራንን፤ አመራሩን እና ሌሎች አጋሮችን በማስተባበርና በልዩ ልዩ ዘርፎች በማደራጀት የሸዋ ብሎም የሃገራችን ህዝብ በማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊና ታሪክን በማበልጸግ ተጠቃሚ እንዲሆን በማድረግ ለሀገር ግንባታ የበኩሉን ሚና እንዲጫወት ማስቻል፡፡ 

የማህበሩ መርሆዎች (VALUES)

  •  አንድነትን ማጠናከር (strengthening unity)

  •  ሰላምን ማረጋገጥ (ensuring peace)

  •  ልማትን መደገፍ (supporting development)

  •  መዋለ ንዋይ ማፍሰስ (investment) 

  •  አካታችነት(inclusiveness) 

  •  መተባበር(cooperation)

  •  ግልጽነት(transparency) 

 •  ተጠያቂነት(accountability) •  ቅንነት(honesty) •  ሃላፊነት(responsiveness)  

Copyright © 2021 Shewa Peace & Development Association  ሸዋ ሰላምና ልማት ማህበር (ሸዋሰማ) - All Rights Reserved.

Powered by GoDaddy Website Builder

  • Privacy Policy