የሚመለከቱትን መመዘኛዎች የሚያሟላ ማንኛውም ሰው የማህበሩ መደበኛ አባል መሆን ይችላል፡፡
1) እድሜው 18 ዓመት እና ከዛ በላይ የሆነ፤
2) ለማህበሩ አላማና ግብ መሳካት እንዲሁም እየገጠሙን ያሉ ችግሮች መፈታት እንዳለባቸው በጽናት የሚያምን፤
3) የመተዳደሪያ ደንቡን እንዲሁም በጠቅላላ ጉባኤውና በስራ አስፈጻሚ የሚወጡ የሥነ-ምግባር ደንቦችን የሚቀበል እና ተግባራዊ የሚያደርግ፣
4) በስራ አስፈጻሚ የተወሰነውን በዓመት 600 ብር አባልነት መዋጮዎች መክፈል የሚችል መሆን አለበት፡፡
5) በህግ ወይም በፍርድ ቤት ውሳኔ መብቱ ያልተገደበ፤
6) ሸዋን ለማገልገል ቁርጠኛ የሆነና ተነሳሽነት ያለው፤
1) የማህበሩ መደበኛ አባል ያልሆኑ ነገር ግን የማህበሩን አላማ ለማስፈጸም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሊያበረከቱ የሚችሉ፤
2) ማህበሩ በሚሰራባቸው ዘርፎች ተሰማርቶ ውጤታማና የለውጥ አርአያ በመሆን በማህበሩ አባላት ተቀባይነትን ያገኙ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች፤
3) የአባልነት መዋጮዎችንና ሌሎች ክፍያዎችን የመክፈል ግዴታ ባይኖርባቸውም፡፡ ነገር ግን መክፈል ከፈለጉ በዓመት 6000 (ስድስት ሺህ ብር) መክፈል አለባቸው፡፡
1. የማህበሩ መደበኛ ወይም ተባባሪ አባል ያልሆኑ ነገር ግን የማህበሩን አላማ ለማስፈጸም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሊያበረከቱ የሚችሉ፤
2. ማህበሩ በሚሰራባቸው ዘርፎች ተሰማርቶ ውጤታማና የለውጥ አርአያ በመሆን በማህበሩ አባላት ተቀባይነትን ያገኙ ድርጅቶች፤
3. የክብር አባላት በራስ ተነሳሽነት ካልሆነ በስተቀር በማህበሩ አመራር አካላት የሚወሰኑ የአባልነት መዋጮዎችንና ሌሎች ክፍያዎችን የመክፈል ግዴታ አይኖርባቸውም፡፡ ነገር ግን መክፈል ከፈለጉ በዓመት12000 (አስራ ሁለት ሺህ ብር) መክፈል አለባቸው፡፡
Copyright © 2021 Shewa Peace & Development Association ሸዋ ሰላምና ልማት ማህበር (ሸዋሰማ) - All Rights Reserved.
Powered by GoDaddy Website Builder